"የዓድዋ ድል በዓል ምኒልክ አደባባይ ይከበራል" የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር
126ኛውን የዓድዋ ድል በዓል በምኒልክ አደባባይ እንደሚያከብር እና ሕዝቡም በተለመደዉ መንገድ በዓሉን በአደባበዩ ለመታደም እንዲገኝ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ገለጸ፡፡
በዓሉ በምኒልክ አደባባይ እንደማይከበር የሚወራዉ ወሬም ከመረጃ ክፍተት እና አለመናበብ የመጣ ነዉ ብሏል ማኅበሩ፡፡
የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ ለአሚኮ እንደተናገሩት የዓድዋ ድልን እና ምኒልክን መለየት አይቻልም፡፡ አጤ ምኒልክ መላ ኢትዮጵያን አስተባብረዉ የበሰለ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አመራር ባይሰጡ ኖሮ የዓድዋ ድል አይኖርም ነበር፤ አጤ ምኒልክ በዓድዋ ድል መሪ ተዋናይ ናቸው ያሉት ፕሬዚዳንቱ ለኢትዮጵያ ብቻም ሳይኾን ለጥቁር ሕዝቦች ኩራት እና የነጻነት ብስራት ስለኾኑ በዓሉ በእሳቸዉ አደባበይ ይከበራል ብለዋል፡፡
በበዓሉም በምኒልክ አደባባይ የአበባ ጉንጉን ይቀመጣል፤ መላ ኢትዮጵያዊያንም ከአሁን በፊት እንደሚከበረዉ በአጤ ምኒልክ አደባበይ ተገኝቶ በዓሉን እንዲታደም ነዉ ጥሪያቸዉን ያስተላለፉት፡፡ (አሚኮ)
አራት የሬዲዮ ብሮድካስት ባለፈቃዶች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለአራት ሬዲዮ ብሮድካስት ባለፈቃዶች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ፡፡
ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው ሬዲዮ ብሮድካስት ባለፈቃዶችም ፣ ሟርሴ መልቲሚዲያ ኃ.የተ.የግ.ማ.(ጄ ሬዲዮ ጣቢያ 106.7 ) ፣ አዲስ ኦንላይን የግንኙነትና የግብይት ሥራ ኃ.የተ.የግ.ማ.(ሀበሻ ኤፍ.ኤም. ሬዲዮ 98.7) ፣ትርታ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ. (ትርታ ሬዲዮ 97.6) እና ኢትዮ ዋርካ መልቲ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን አ.ማ (ዋርካ ሬዲዮ 104.1) መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ባለስልጣኑ ጉዳዩን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው ማብራሪያ፥ ጄ ሬዲዮ ጣቢያ 106 ነጥብ 7 የተሰኘው ባለፈቃድ የሬድዮ ፈቃዱን ካገኘ ጀምሮ ሙዚቃ ብቻ በማጫወት በውድድር ፈቃድ ከወሰደበት ውል ውጪ እየሰራና ውስን የሆነውን የሬድዮ ሞገድ ከታለመለት አላማ ውጪ ለብክነት እየዳረገ ይገኛል ብሏል፡፡
በውድድር የሚገኝን ይህን ውድ የሀገርና የህዝብ ሀብት ለተፈቀደው እና ውል ለተገባበት አላማ እንዲውል በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በተደጋጋሚ ጊዜ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ቢሆንም በድርጅቱ በኩል የተለወጠ ነገር አለመኖሩ ተጠቁሟል፡፡
ስለዚህም ሬድዮ ጣቢያው እስከ መጋቢት 01 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ውል በገባው መሰረት መደበኛ ስርጭቱን ካልጀመረ ፈቃዱ በቀጥታ እንደሚሰረዝ ባለስልጣኑ አስጠንቅቋል፡፡
በሌላ በኩል አዲስ ኦንላይን፣ ትርታ ትሬዲንግ እና ኢትዮ ዋርካ የተሰኙ ድርጅቶች በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 80 መሠረት ከባለሥልጣን መ/ቤቱ የንግድ ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ ወስደው ከአንድ ዓመት በላይ ቢሞላቸውም በህጉ መሰረት መደበኛ ስርጭት ባለመጀ
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል ይኸን ብለዋል:-
"በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራር ስነ ስርዓት ደንብ መሰረት አንድ አባል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ ለማቅረብ ከ10 ቀን በፊት ለአፈ ጉባዔ ጽ/ቤት ማስገባት ይጠበቃል።
ከዚያም ከአባላት የተሰበሰቡትን ጥያቄዎች አፈጉባኤዎችና በፓርላማው የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተሰባስበው የሚፈልጓቸውን ይመርጣሉ። የተመረጡ ጥያቄዎች ለጠ/ሚ/ሩ ይቀርባሉ ማለት ነው።
ከታች የተያያዙትን ጥያቄዎች ለጠቅላይ ሚኒሰረትሩ ለማቅረብ ከ15 ቀን በፊት ብናስገባም የገዢው ፓርቲ መቀስ ቆርጦ አስቀርቷቸዋል። ፓርላማው በብዙ አፋኝ ህገ ደንቦችና አሰራሮች መተብተቡና ሰፊ የአሰራር ማሻሻያዎችን እንደሚያስፈልግ አመላካች ነው።
ሌላው አስገራሚ ጉዳይ መስከረም 23 ላይ የቀረበ የክብርት ፕሬዚዳንቷ የመክፈቻ ንግግር ላይ ሞሽን የቀረበው የበጀት አመቱ ሊጠናቀቅ 4 ወር ሲቀረው መወያየቱ አስተዛዛቢ ነው።"
የአርቲስት ኒና ግርማ ማጀቴ የሙዚቃ አልበም ነገ ይለቀቃል
"ማጀቴ" የተሰኘው አዲስ የሙዚቃ አልበም በመጪው ሐሙስ ለአድማጭ ይደርሳል።
በሻኩራ ሪከርድስ የተዘጋጀው "ማጀቴ" የተሰኘው አልበም ሀሙስ የካቲት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ለአድማጭ እንደሚደርስ አዘጋጆቹ ትላንት በቀነኒሳ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርገዋል።
ይህ አልበም የራፕ ዘፈኖችን በማቀንቀን የምትታወቀው ኒና ግርማ የመጀመሪያ አልበም ሲሆን፥ በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ስራዎችንም አካቷል።
በካሙዙ ካሳ የተቀናበረው የማጀቴ አልበም የግጥም እና ዜማ ድርሰት በኒና ግርማ የተሰራ እንደሆነና በሻኩራ ሪከርድስ አማካይነት ፕሮዲዩስ እንደተደረገም ተገልጿል።
20 የታሸገ ውሀ አምራቾች በግብአት እጥረት እና የዋጋ ንረት ምክንያት ሥራ አቆሙ
የኢትዮጲያ የታሸገ ውሀ እና ለስላሳ መጠጥ አምራቾች ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ መርዕድ ለኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ እንደገለጹት በታሸገ ውሀ ዘርፍ 106 ኢንዱስትሪዎች ይገኛሉ፡፡እነዚህ ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ መካከለኛ እና ዝቅተኛ አምራቾችን ያቀፉ ናቸው፡፡
የታሸገ ውሀ አምራች ዘርፍ ከፍተኛ የስራ እድል የፈጠረ ከመሆኑም ባሻገር ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ያሉበት መሆኑን አቶ አሸናፊ ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ የግብአት እጥረት እና የዋጋ መናር በኢንዱስትሪዎቹ እንቅስቃሴ ላይ አደጋ እንዲጋረጥ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡
ማህበሩ በዘርፉ ያጋጠሙትን ችግሮችን በጥናት ለይቶ ለኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ለአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በአካል እና በደብዳቤ የእንነጋገር ጥያቄ ቢያቀርብም ምላሽ አለማግኘቱን አቶ አሸናፊ ገልጸዋል፡፡ በተጠቀሱት ችግሮች ምክንያትም እስካሁን 20 የታሸገ ውሀ አምራቾች ስራ ማቆማቸውን አስታውቀዋል፡፡
ለአብነትም ፒኢፒ የተሰኘው ግብአት ከአንድ አመት ከሶሰት ወራት በፊት በኪ.ግ 53 ብር ሲሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በኪ.ግ 130 ብር ገብቷል ይህም ከእጥፍ በላይ ጭማሪ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አሸናፊ ችግሩ ከግብአቱ አምራች ኩባንያዎች ወይስ ከአስመጪዎቹ ነው የሚለውን ለመለየት እና መፍትሔ ለማስቀመጥ ቢሞከርም በሚመለከታቸው የመንግስት መ/ቤቶች በኩል ተገቢው ትብብር አልተገኘም ብለዋል፡፡
የነዳጅ ዋጋ መጨመር ለዚህ አስተዋጽኦ እንዳለው ቢታመንም አግባብ የሆነውን አካሔድ ለመወሰን እንዲያስችል ከሚመለከታቸው ጋር ውይይት ማድረጉ ወሳኝ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
አብዛኞቹ የውሀ አምራች ኢንዱስትሪዎች በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮሚያ
ኢትዮጵያዊው ዳኛ ባምላክ ተሰማ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚደረገውን ወሳኝ ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመራል
ኢትዮጵያዊው ዳኛ ባምላክ ተሰማ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚደረገውን ወሳኝ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በዋና ዳኝነት እንደሚመራ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስታወቀ።
33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለግማሽ ፍጻሜ ያለፉ አራት አገራት ነገ እና ከነገ በስቲያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን፤ በነገው እለት ምሽት አራት ሰዓት ቡርኪናፋሶ ከሴኔጋል ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ካፍ እንዳስታወቀው፤ ለፍጻሜ ለማለፍ የሚደረገውን ይህን ጨዋታ ኢትዮጵያዊው ዳኛ ባምላክ ተሰማ በዋና ዳኝነት ይመራዋል፡፡
በተጨማሪ ሱዳናዊው ሙሀመድ አብዱላሂና ኬኒያዊው ጊልበርት ችሮይት ደግሞ በረዳትነት ዳኝነት ጨዋታውን የሚመሩት ይሆናል፡፡
ከነገ በስቲያ ምሽት አራት ሰዓት ደግሞ የውድድሩ አስተናጋጅ ካሜሩን እና ግብጽ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ይታወቃል፡፡(ENA)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የተሳካ ሙከራ አካሄደ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሶስት ዓመታት በኋላ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የመጀመሪያ የሙከራ በረራ በተሳካ ሁኔታ ማከናወኑን አስታወቀ።
አየር መንገዱ የሙከራ በረራውን ያከናወነው ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ባካሔደው የደርሶ መልስ በረራ እንደሆነም ተገልጿል።
ለሙከራ በረራውም እ.አ.አ በ2018 የቦይንግ አውሮፕላን በረራ መቆጣጠሪያ ክፍሉ ላይ በታየው የቴክኒክ ችግር ምክንያት አደጋ ከተከሰተ በኋላ የበረራ አገልግሎት እንዳይሰጡ ከታገዱት አውሮፕላኖች መካከል ቦይንግ 737 ET-AVI ET 9201 የተባለ አውሮፕላን መጠቀሙንም ጨምሮ ጠቅሷል።
በረራውም ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሶ መልስ የተከናወነ ስለመሆኑም መረጃው አመላክቷል።
ሙከራው የቦይንግ አውሮፕላን በቴክንክ ችግር ምክንያት ለአደጋ ተጋልጦ ለበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፍ እና ንብረት ውድመት ምክንያት ከሆነው አደጋ በኋላ የተደረገ የመጀመሪያው መሆኑም ተገልጿል።
እንዲህ አይነቱ የሙከራ በረራ የቦይንግ አውሮፕላን ወደ መደበኛ የበረራ አገልግሎት እንዲመለስ ለማድረግ አይን ገላጭ ሆኖ ያገለግላል ተብሏል።
አየር መንገዱ ከቀናት በኋላ የቦይንግ አውሮፕላኖቹን ወደ በረራ ሊመልስ ስለመሆኑ ኢዜአ መዘገቡ ይታወሳል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አጸደቀ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፌዴራል መንግሥት የ2014 በጀት ዐመት የቀረበለትን 122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ። በጀቱ በኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት ተጨማሪ ወጪ በማስፈለጉ፤ የሚሰበሰበው ገቢ አሁን ያለውን የክፍያ ጥያቄ ለማስተናገድ አስቸጋሪ ሁኔታ በመፍጠሩ፤ እንዲሁም ወቅቱ የፈጠረውን የተጨማሪ ወጪ ፍላጎት በበጀት ሽግሽግ ለማስተናገድ ባለመቻሉ መቅረቡ ተገልጿል። ተጨማሪ በጀቱን በሀገር ውስጥ ብድር ለመሸፈን ታሳቢ መደረጉም ተነግራል። በዚህ መሰረት ለመከላከያ ለትጥቅ እና ቀለብ 90 ቢሊዮን ብር፣ ለዜጎች የዕለት የስንዴ እና አልሚ ምግብ ግዥ 8 ቢሊዮን ብር፣ በጦርነት የወደሙ መሠረተ ልማቶችን እና አገልግሎቶችን መልሶ የመገንባት ሥራ ለማስጀመር ከመንግሥት ግምጃ ቤት 5 ቢሊዮን ብር ተደግፎ መቅረቡ ተገልጿል። ለመልሶ ግንባታ የተመደበው ገንዘብ አንሷል የሚሉ ጥያቄዎች ከምክር ቤት አባላት በስፋት ተጠይቋል። የገንዘብ ሚኒስቴር፦ ገንዘቡ ሥራውን ለማስጀመር እንጂ በቂ ነው የሚል አቋም እንደሌለ፤ ሆኖም በሂደት የመልሶ ግንባታ ተግባሩ በልዩ ልዩ አሠራር ታግዞ እንደሚከናወን ምላሽ ሰጥቷል። የተጨማሪ በጀትና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያው በዘጠኝ ተቃውሞ፣ በሰባት ድምፅ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።
ዘገባ፦ ሰለሞን ሙጬ ዶይቸ ቬለ (DW) አዲስ አበባ
በነገው ዕለት በድሬዳዋ ለሚቀጥለው ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በሁሉም ዘርፍ ዝግጅት መጠናቀቁን የድሬዳዋ አስተዳደርና የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ
ለቤቲንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ የመጡ የእግር ኳስ ቤተሰቦች በሙሉ ፍቅር ወደሆነችው ከተማችን ድሬዳዋ እንኳን በሰላም መጣችሁ ብለዋል ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳርን በመወከል ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ የለውጡ አመራር በሁሉም ዘርፍ ድሬዳዋን ወደ ቀድሞ ከፍታዋ ለመመለስ በተያዘው አቅጣጫ በልዩ ትኩረት የውድድሩን በመመራቱ ዝግጀቱ መጠናቀቁን አሳውቀዋል ፡፡
ቤተኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በድሬዳዋ መከናወኑ ዘርፈብዙ የሆኑ (ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና የድሬዳዋን መልካም ገጽታ )ከመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው የገለጹት ኃላፊው የስፖርት ቤተሰቡ በድሬዳዋ በሚኖረው ቆይታ የድሬዳዋን የአብሮነት ፣ መደጋገፍና የፍቅር መናሀርያ መሆኗን ትዝታ ፈጥሮበት በሰላም እንዲመለስ የተለያዩ ሁነቶች በመሀል በመሀል ተዘጋጅተዋል ብለዋል ፡፡
ጸጥታን በሚመለከት ድሬዳዋ በቀርቡ ባሳለፍነው በዓል ዓለምን ማስደመም የቻለችበትን አጋጣሚ ተሞክሮ በማጠናከር ለስድስት ሳምንት የሚቆየው ውድድር ያለ ኮሽታ አእንዲጠናቀቅ ሁሉም የጸጥታ አካሎቻችን ዝግጅትተጠናቋል ሲሉ አቶ ህዝቅያስ የጸጥታ አካሉን ዝግጅት አረጋግጠዋል ፡፡
በመጨረሻም የበትኪንግ አመራሮችና ባለሙያዎች ፣ የየቡድኑ አመራሮችና ተጫዋቾች፣የሚዲያ አካላትና እንግዶች በድሬዳዋ የሚኖራቸው ቆይታ ያማረና የስኬት እንዲሆን ተመኝተዋል ፡፡
የወጣቶችን ስፖር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍራውል ቡልቻ በስፖረቱ ዘርፍ የተደረጉ ዝግግቶች
ድል ለዋልያዎቹ !
የ2021 አፍሪካ ዋንጫ ዛሬ በይፋ ይጀመራል። ሀገራችን ኢትዮጵያም የምድቡ የመጀመርያ ጨዋታዋን ምሽት 4፡00 ላይ ከኬፕ ቨርድ ጋር ታደርጋለች።
ከኢትዮጵያ እና ኬፕ ቨርድ ጨዋታ ቀደም ብሎ በምድባችን የሚገኙት አስተናጋጇ ካሜሩን እና ቡርኪና ፋሶ የመክፈቻ ጨዋታቸውን ምሽት 1፡00 ሰዓት ላይ እንደሚያከናውኑ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የተገኘ መረጃ ይጠቁማል።
ድል ለዋልያዎቹ !
ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተሰጣቸው።
የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተሰጣቸው።
ዛሬ በተካሄደ ስነስርዓት ፥ ውጊያ ለመሩ ፣ ሀይል ለመሩ ፣ ድልና ውጤት ላስገኙ ከፍተኛ የጦሩ መኮንኖች በየደረጃው የማዕረግ ዕድገት ተሰጥቷል።
በዚህም መሰረት 1 የፍልድ ማርሻል ማዕረግ ፣ 4 የሙሉ ጀነራል ማዕረግ ፣ 14 የሌተናል ጀነራል ማዕረግ፣ 24 የሜጀር ጀነራል ማዕረግ እና 58 የብርጋዴር ጀነራል ማዕረግ ተሰጥቷል።
የጀነራል መኮንኖቹ ሹመት በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አብይ አሕመድ አቅራቢነት በርዕሰ ብሄር ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ነው የተሰጠው። ዘገባው የፋብኮ ነው
የመከላከያ ሠራዊቱ ሲጠቀምበት በቆየው የማዕረግ ምልክት ላይ ማሻሻያዎችን አደረገ።
የመከላከያ ሠራዊቱ ሲጠቀምበት በቆየው የማዕረግ ምልክት ላይ ማሻሻያዎችን አድርጓል። ማሻሻያው የተደረገበት ምክንያትም የሠራዊቱ ማዕረግ አገራዊም ይሁን ወታደራዊ ታሪካዊ ይዘት ያለውና የሠራዊቱንም ባህሪ ሊገልፅ የሚችል ሆኖ እንዲዘጋጅ በማስፈለጉ ነው።
በዚህም መሠረት በሠራዊታችን የማዕረግ ምልክቶች ውስጥ ጋሻና አንበሳ በዋናነት ጥቅም ላይ ውለዋል።
በአገራችን የቀደመ ታሪክም በተለይ ጋሻው በንጉሱም ይሁን በደርግ ዘመን በሠራዊቱ የማዕረግ ምልክቶች ላይ ጥቅም ላይ ውሏል። ንጉሱ ዘውድን በማዕረግ ምልክትነት ሲጠቀሙ፣ ደርግ ዘውዱን መቀየር ስለነበረበት ዘውዱን በአንበሳ ተክቶ ተጠቅሞበታል። እነዚህ ሁለቱም ታሪካዊና ወታደራዊ ምልክቶች ናቸው።
አሁን ስንጠቀምበት የቆየው የሠራዊቱ ማዕረግ እነዚህን ምልክቶች በመሰረታዊነት ነበር የቀየራቸው። በርግጥም ሲታይ ታሪካዊና አገራዊ ይዘቱ የጎላ አልነበረም። ሠራዊት ዘመን ተሻጋሪ መሆን ካለበት ዓርማውም
በጋና የቁንጅና ውድድር ኢትዮጵያን በመወከልና በማስተዋወቅ የተሳተፈችው ጋናዊት አዲስ አበባ ገባች
በጋና የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ባህል በመወከልና በማስተዋወቅ የተሳተፈችው ዶክተር ሴቶር ኖርግቤ አዲስ አበባ ገባች።
ጋናዊቷ የሜዲካል የአዕምሮ ህክምና ባለሙያና ደራሲ ዶክተር ሴቶር ኖርግቤ የኢትዮጵያን ታሪክ ፤ስልጣኔ፤ባህላዊ አልባሳት በጋና የቁንጅና መድረክ ላይ በማስተዋወቅ የሀገሯን የቁንጅና ውድድር የመጀመሪያ ዙር ማሸነፏ ይታወቃል።
በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥሪ መሰረት በርካታ ዳያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት እየገቡ ይገኛሉ በዚህ ጥሪ የኢትዮጵያ ወዳጆችና አፍሪካውያን ጭምር እየተሳተፉ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ይገኛል።
በሀገሯ ጋና የቁንጅና ውድድር ላይ ኢትዮጵያን በማስተዋወቅ ለኢትዮጵያ ያላትን ልዩ ፍቅር የገለጸቸው ጋናዊቷ የሜዲካል የአዕምሮ ህክምና ባለሙያና ደራሲ ዶክተር ሴቶር ኖርግቤ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብታለች።
የኢትዮጵያ ወዳጇ ዶክተር ሴቶር በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትደርስም በታዋቂ ሰዎ
በአገር አቀፍ ደረጃ አዲስ የኮቪድ-19 ማዕበል መከሰቱን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አስታወቀ
በአገር አቀፍ ደረጃ አዲስ የኮቪድ-19 ማዕበል መከሰቱን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አስታውቋል፡፡
ኢንስቲቲዩቱ ሰሞኑን በተከሰተው ጉንፋን መሰል ወረርሽኝ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
በማብራሪያውም ሰሞኑን የተከሰተውን ጉንፋን መሰል ወረርሽኝን ተከትሎ በአንዳንድ ተቋማት በተወሰደ የናሙና ምርመራ ከ59 እስከ 86 በመቶ የሚሆኑት የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ጠቁሟል፡፡
ኢንስቲቲዩቱ ባለፉት 15 ቀናትም በተለይ በአዲስ አበባ የኮቪድ-19 ስርጭት በስፋት መስተዋሉን ነው የገለጸው፡፡
ወደጤና ተቋማት ሄደው ከተመረመሩት ከ55 ሺህ በላይ ሰዎች ከ25 ሺህ በላይ የሚሆኑት ኮቪድ-19 እንደተገኘባቸው ተመላክቷል፡፡
እንደ አገር ከሁለት ሳምንት በፊት 5 በመቶ የነበረው በኮቪድ19 የመያዝ ምጣኔ አሁን ላይ ወደ 36 በመቶ ከፍ ማለቱም በማብራሪያው ተጠቁሟል፡፡
ዜጎች "የጉንፋን ወረረሽኝ" ከሚለው መዘናጋት