አምባሳደር ታዬ አንቀጸሥላሴ የተባበሩት መንግሥታትን ሚዛን የሳተ ወቀሳ ተቹ
አሸባሪው ሕወሓት እርዳታ ጭነው ትግራይ የገቡ 1 ሺሕ 10 ተሽከርካሪዎችን ጠልፎ ለጦርነቱ ሲጠቀም የተስማማ በሚመስል መልኩ ዝምታን የመረጠው የተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ወታደሮች 3 ተሽከርካሪዎቼን መጠቀማቸውን አወግዛለሁ ሲል መደመጡ ተገቢነት እንደሌለው በመንግሥታቱ ኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ተቹ፡፡
አምባሳደር ታዬ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ቃል አቀባይ የሰጠውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም እንቅስቃሴ የተመለከተ መግለጫ ጠቅሰው ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ወታደሮች 3 የመንግሥታቱን ተሽከርካሪዎችን አዘዋል በሚል ለተሰማው ያልተረጋገጠ ወሬ ፈጥኖ የውግዘት መግለጫን ላወጣው የተባበሩት መንግሥታት የሽብር ቡድኑ 1 ሺሕ 10 ተሽከርካሪዎችን ጠልፎ እስካሁንም በይፋ ሲጠቀምባቸው ምንም ያላለ ድርጅት መሆኑን አስታውሰውታል፡፡ (1/2)
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የፌደራል መንጃ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት መስጠት ጀመረ
በአዲሱ የተቋማት አደረጃጀት መሰረት ቀደም ሲል በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ሲሰራ የነበረው የፌደራል መንጃ ፈቃድ እድሳት ከጥቅምት 5/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ በውክልና ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት ከህዳር 23/2014 ዓ.ም ጀምሮ የፌደራል መንጃ ፈቃድ እድሳት ከዚህ ቀደም አገልግሎቱ ይሰጥበት በነበረበት በቃሊቲ የአሽከርካሪዎች የማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ አገልግሎቱን መስጠት የጀመረ በመሆኑ ተገልጋዮች አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ቢሮው አሳውቋል፡፡ #Ethiopia #MejaFikad #AddisAbaba