አምባሳደር ታዬ አንቀጸሥላሴ የተባበሩት መንግሥታትን ሚዛን የሳተ ወቀሳ ተቹ

አሸባሪው ሕወሓት እርዳታ ጭነው ትግራይ የገቡ 1 ሺሕ 10 ተሽከርካሪዎችን ጠልፎ ለጦርነቱ ሲጠቀም የተስማማ በሚመስል መልኩ ዝምታን የመረጠው የተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ወታደሮች 3 ተሽከርካሪዎቼን መጠቀማቸውን አወግዛለሁ ሲል መደመጡ ተገቢነት እንደሌለው በመንግሥታቱ ኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ተቹ፡፡

አምባሳደር ታዬ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ቃል አቀባይ የሰጠውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም እንቅስቃሴ የተመለከተ መግለጫ ጠቅሰው ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ወታደሮች 3 የመንግሥታቱን ተሽከርካሪዎችን አዘዋል በሚል ለተሰማው ያልተረጋገጠ ወሬ ፈጥኖ የውግዘት መግለጫን ላወጣው የተባበሩት መንግሥታት የሽብር ቡድኑ 1 ሺሕ 10 ተሽከርካሪዎችን ጠልፎ እስካሁንም በይፋ ሲጠቀምባቸው ምንም ያላለ ድርጅት መሆኑን አስታውሰውታል፡፡ (1/2)