ሱዳናውያን ወታደራዊ መንግስታቸውን መቃወማቸውን ቀጥለዋል
ሱዳናውያን ወታደራዊ መንግስታቸውን በመቃዎም አሁንም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል፡፡
ባለፈው አመት የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን በካርቱም ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግስት ፊት ለፊት ባደረጉት ሰልፍ አንድ ሱዳናዊ ተቃዋሚ በጥይት ተመትቶ መሞቱን የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል።
ጄኔራል አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን ባለፈው አመት ጥቅምት 25 ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ካደረጉ በኋላ በተደረጉ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፎች የሞቱ ሰዎች ቁጥር 84 መድረሱን ገለልተኛ የህክምና ባለሙያዎች ቡድን አስታውቋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰባዊ መብት ባለሙያ የሆኑት አዳማ ዲንግ ወደ ሱዳን በሄዱበት ወቅት የሱዳን ባለሥልጣናት በተቃዋሚዎች ላይ የሚወስዷቸው እርምጃዎች እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በተመሳሳይ የሱዳን ተቃዋሚዎች ጉዳይ እንደሚያሳስበው የገለፀ ሲሆን ሁከቱ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ተጨማሪ መዘዞች ሊመጡ እንደሚችሉ ያለውን ስጋት ገልጿል፡፡
የሱዳን የቅርብ ጊዜ መፈንቅለ መንግሥቱ ሰፊ ዓለም አቀፍ ውግዘት እያጋጠመው ሲሆን ሀገሪቱ ያላት ዲፕሎማሲየዊ ግንኙነት እንዲቀዛቀዝ ምክንያት መሆኑን አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አስታውቋል፡፡ (ኤፍ ቢሲ)
"የዓድዋ ድል በዓል ምኒልክ አደባባይ ይከበራል" የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር
126ኛውን የዓድዋ ድል በዓል በምኒልክ አደባባይ እንደሚያከብር እና ሕዝቡም በተለመደዉ መንገድ በዓሉን በአደባበዩ ለመታደም እንዲገኝ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ገለጸ፡፡
በዓሉ በምኒልክ አደባባይ እንደማይከበር የሚወራዉ ወሬም ከመረጃ ክፍተት እና አለመናበብ የመጣ ነዉ ብሏል ማኅበሩ፡፡
የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ ለአሚኮ እንደተናገሩት የዓድዋ ድልን እና ምኒልክን መለየት አይቻልም፡፡ አጤ ምኒልክ መላ ኢትዮጵያን አስተባብረዉ የበሰለ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አመራር ባይሰጡ ኖሮ የዓድዋ ድል አይኖርም ነበር፤ አጤ ምኒልክ በዓድዋ ድል መሪ ተዋናይ ናቸው ያሉት ፕሬዚዳንቱ ለኢትዮጵያ ብቻም ሳይኾን ለጥቁር ሕዝቦች ኩራት እና የነጻነት ብስራት ስለኾኑ በዓሉ በእሳቸዉ አደባበይ ይከበራል ብለዋል፡፡
በበዓሉም በምኒልክ አደባባይ የአበባ ጉንጉን ይቀመጣል፤ መላ ኢትዮጵያዊያንም ከአሁን በፊት እንደሚከበረዉ በአጤ ምኒልክ አደባበይ ተገኝቶ በዓሉን እንዲታደም ነዉ ጥሪያቸዉን ያስተላለፉት፡፡ (አሚኮ)
የሩሲያ እና ዩክሬን የሰላም ድርድር ዛሬ በቤላሩስ ይጀመራል
የሩሲያ እና ዩክሬን የሰላም ድርድር በዛሬው እለት በቤላሩስ እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡
በቤላሩስ የሚደረገው የሁለቱ አገራት የሰላም ድርድር በዩክሬን የሩሲያ ወታደራዊ ዘመቻን ለማስቆም ያለመ ስለመሆኑ ተመላክቷል፡፡
ብዙ የሩሲያ ቋንቋ ተናጋሪዎች ያሏቸውን የዶኔትስክ እና የሉጋንስክ ግዛቶችን ከጸረ-ሩሲያውያን ለመጠበቅ በሚል ሞስኮ በዩክሬን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን ይዟል፡፡
ከወታደራዊ ዘመቻው ጥቂት ቀናት በኋላ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ÷ አገራቸው ከሩሲያጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆኗን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎም የሚደረገው ድርድር በአገራቱ መካከል የተጀመረውን ጦርነት ማስቆም ያስችላል በሚል በተስፋ ሲጠበቅ ቆይቷል፡፡
እንደ አር ቲ ዘገባ አገራቱ በዛሬው ዕለት የሰላም ድርድሩን የሚጀምሩ ሲሆን÷ ምክክሩም ከዩክሬን ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ቤላሩስ ከሰዓታት በኋላ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የቤላሩስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም የአገራቱን የሰላም ድርድር ለማስጀመር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጓን አስታውቋል::(ኤፍ ቢ ሲ)
"የአድዋን ታሪክ በሚገባ በመለየት አሁን ላለንበት ችግር መፍቻ ቁልፍ ማድረግ ይገባል" - ሂሩት ካሳው (ዶክተር)
የአድዋን ታሪክ በሚገባ በመለየት አሁን ላለንበት ችግር መፍቻ ቁልፍ ማድረግ ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነጥበባትና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶክተር) ገለጹ።
የአድዋ ድል በዓል ለ126ኛ ጊዜ “አድዋን ለኢትዮጵያውያን ኅብረት፣ ለአፍሪካ የነፃነት ጮራ” በሚል መሪ ሃሳብ የሚከበረውን በአል አስመልክቶ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
በዚህ መድርክ ላይ የቢሮዉ ሃላፊው እንደገለጹት፣ አድዋ የነጻነት ድል ብቻ ሳይሆን ፍትህ፣ አርነት፣ ሉአላዊነት የተገኘበት ድል ነው። ይህን በተለየ መንገድ ማየት መጠቀም ያስፈልጋል።
እንደ ዶክተር ሂሩት ንግግር፣ አድዋ ኢትዮጵያ ለአለም ፍትህን ያሳየችበትና በአለም እይታ ውስጥ የገባችበት ድል ነው።
ስለዚህ አድዋን በሚገባ በመረዳት አሁን ላለንበት ችግር የመፍቻ ቁልፍ አድርጐ መጠቀም ያስፈልጋል።
በፓናል ውይይቱ ከአድዋ ምን መማር አለብን፣ ከአድዋ በኋላ ኢትዮጵያ ምን አገኘች፣ ምን ሆነች የሚሉ ጉዳዮችን በጥናታዊ ጹሁፍ ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሏል።
በውይይቱ አባትና እናት አርበኞች፣ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተወካዮችና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።(ኢ.ፕ.ድ)
አራት የሬዲዮ ብሮድካስት ባለፈቃዶች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለአራት ሬዲዮ ብሮድካስት ባለፈቃዶች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ፡፡
ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው ሬዲዮ ብሮድካስት ባለፈቃዶችም ፣ ሟርሴ መልቲሚዲያ ኃ.የተ.የግ.ማ.(ጄ ሬዲዮ ጣቢያ 106.7 ) ፣ አዲስ ኦንላይን የግንኙነትና የግብይት ሥራ ኃ.የተ.የግ.ማ.(ሀበሻ ኤፍ.ኤም. ሬዲዮ 98.7) ፣ትርታ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ. (ትርታ ሬዲዮ 97.6) እና ኢትዮ ዋርካ መልቲ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን አ.ማ (ዋርካ ሬዲዮ 104.1) መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ባለስልጣኑ ጉዳዩን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው ማብራሪያ፥ ጄ ሬዲዮ ጣቢያ 106 ነጥብ 7 የተሰኘው ባለፈቃድ የሬድዮ ፈቃዱን ካገኘ ጀምሮ ሙዚቃ ብቻ በማጫወት በውድድር ፈቃድ ከወሰደበት ውል ውጪ እየሰራና ውስን የሆነውን የሬድዮ ሞገድ ከታለመለት አላማ ውጪ ለብክነት እየዳረገ ይገኛል ብሏል፡፡
በውድድር የሚገኝን ይህን ውድ የሀገርና የህዝብ ሀብት ለተፈቀደው እና ውል ለተገባበት አላማ እንዲውል በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በተደጋጋሚ ጊዜ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ቢሆንም በድርጅቱ በኩል የተለወጠ ነገር አለመኖሩ ተጠቁሟል፡፡
ስለዚህም ሬድዮ ጣቢያው እስከ መጋቢት 01 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ውል በገባው መሰረት መደበኛ ስርጭቱን ካልጀመረ ፈቃዱ በቀጥታ እንደሚሰረዝ ባለስልጣኑ አስጠንቅቋል፡፡
በሌላ በኩል አዲስ ኦንላይን፣ ትርታ ትሬዲንግ እና ኢትዮ ዋርካ የተሰኙ ድርጅቶች በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 80 መሠረት ከባለሥልጣን መ/ቤቱ የንግድ ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ ወስደው ከአንድ ዓመት በላይ ቢሞላቸውም በህጉ መሰረት መደበኛ ስርጭት ባለመጀ
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል ይኸን ብለዋል:-
"በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራር ስነ ስርዓት ደንብ መሰረት አንድ አባል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ ለማቅረብ ከ10 ቀን በፊት ለአፈ ጉባዔ ጽ/ቤት ማስገባት ይጠበቃል።
ከዚያም ከአባላት የተሰበሰቡትን ጥያቄዎች አፈጉባኤዎችና በፓርላማው የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተሰባስበው የሚፈልጓቸውን ይመርጣሉ። የተመረጡ ጥያቄዎች ለጠ/ሚ/ሩ ይቀርባሉ ማለት ነው።
ከታች የተያያዙትን ጥያቄዎች ለጠቅላይ ሚኒሰረትሩ ለማቅረብ ከ15 ቀን በፊት ብናስገባም የገዢው ፓርቲ መቀስ ቆርጦ አስቀርቷቸዋል። ፓርላማው በብዙ አፋኝ ህገ ደንቦችና አሰራሮች መተብተቡና ሰፊ የአሰራር ማሻሻያዎችን እንደሚያስፈልግ አመላካች ነው።
ሌላው አስገራሚ ጉዳይ መስከረም 23 ላይ የቀረበ የክብርት ፕሬዚዳንቷ የመክፈቻ ንግግር ላይ ሞሽን የቀረበው የበጀት አመቱ ሊጠናቀቅ 4 ወር ሲቀረው መወያየቱ አስተዛዛቢ ነው።"
በአፋር የተከፈተው ጥቃት የኢትዮጵያን ገጽታ ለማጠልሸት ያለመ ነው₋ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ሰሞኑን በአሸባሪው ህወሃት በአፋር የተከፈተው ጥቃት ዋናኛ አላማ የኢትዮጵያን ገጽታ ለማጠልሸት ያለመ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝብ ተወካዮች ለቀረቡ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ አሸባሪው እና ቁማርተኛው ህወሃት የአለም ሀገራት ኢትዮጵያን ለመክሰስ ያስችላል በሚል ጥቃቱን መክፈቱን ገልጸዋል፡፡
በአፋር የተከፈተው ጥቃት የመላው ኢትዮጵያውን ጥቃት በመሆኑ በጋራ እንከላከለዋለንም ብለዋል፡፡
ለትግራይ ህዝብ ምግብ እና መድሃኒት አለመድረሱ ምንም ደንታ ያሌለው ህወሃት ዋነኛ ስሌቱ ያራሱ ጥቅም ብቻ ማስጠበቅ መሆኑን በግልጽ አሳይቷል ብለዋል፡፡
የአፋር እና የአማራ ህዝብ በወንድም ትግራይ ህዝብ ላይ መንገድ ለመዝጋት ቀርቶ የአሸባሪውን ህወሃት ቁስለኞችን በመንከባከብ ሞራል ያለው ህዝብ መሆናቸውን አሳይተዋል ብለዋል፡፡
በዚህ ጦርነት እንደ ትግራይ ክልል የደቀቀ ክልል የለም የሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢትዮጵያ ህዝብ ትግራይን መልሶ የመገንባት ዕዳ አለበት ብለዋል፡፡(EBC)
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ምስጋና አቀረቡ
የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በህልውና ዘመቻው ወቅት በግንባር ዘምተው ላበረከቱት አስተዋጾ ምስጋና አቅርበዋል።
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ያሉት የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄያቸው ከማቅረባቸው አስቀድመው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በህልውና ዘመቻው ወቅት ግንባር ዘምተው የአገር አንድነትን ለማስጠበቅ ለከፈሉት ዋጋ ምስጋና አቅርበዋል።
ብዙዎቻችን ኢትዮጵያን እንወዳለን እንላለን እርስዎም ይላሉ እርስዎ ግን በተጨባጭ ግንባር ዘምተው የአገር አንድነትን ያስጠበቁ ስለሆነ ምስጋና ይገባዎታል ሲሉም አባላቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል።
በአሁኑ ወቅት የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄያቸውን እያቀረቡ ናቸው።
(ኢ ፕ ድ)
የአርቲስት ኒና ግርማ ማጀቴ የሙዚቃ አልበም ነገ ይለቀቃል
"ማጀቴ" የተሰኘው አዲስ የሙዚቃ አልበም በመጪው ሐሙስ ለአድማጭ ይደርሳል።
በሻኩራ ሪከርድስ የተዘጋጀው "ማጀቴ" የተሰኘው አልበም ሀሙስ የካቲት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ለአድማጭ እንደሚደርስ አዘጋጆቹ ትላንት በቀነኒሳ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርገዋል።
ይህ አልበም የራፕ ዘፈኖችን በማቀንቀን የምትታወቀው ኒና ግርማ የመጀመሪያ አልበም ሲሆን፥ በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ስራዎችንም አካቷል።
በካሙዙ ካሳ የተቀናበረው የማጀቴ አልበም የግጥም እና ዜማ ድርሰት በኒና ግርማ የተሰራ እንደሆነና በሻኩራ ሪከርድስ አማካይነት ፕሮዲዩስ እንደተደረገም ተገልጿል።
ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ “ለዓመቱ ምርጥ የአፍሪካ ወጣት” ሽልማት በእጩነት ቀረቡ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ “በፊውቸር አፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ወጣት” ሽልማት ውስጥ በእጩነት ቀረቡ።
አፍሪካውያን ወጣቶችን በማስተሳሰር የአህጉሪቷን ችግሮች ለመቅረፍ የሚንቀሳቀሰው “ዘ ፊውቸር አፍሪካ” ፕሮጀክት የ16ተኛውን ዘ ፊውቸር ሽልማት እጩዎችን ይፋ አድርጓል።
ታዋቂው የእግር ኳስ ተጫዋች ሞሐመድ ሳላህን ጨምሮ አምስት አፍሪካውያን በተካተቱበት የእጩዎች ዝርዝር ውስጥ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜም ተካተዋል።
ለሽልማቱ በእጩነት መመረጣቸውን ተከትሎ ኮሚሽነሯ ባስተላለፉት መልዕክት “በሽልማቱ እጩ ዝርዝር ውስጥ በመካተቴ ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል፣ ለፕሮጀክቱም ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ብለዋል።
በእጩነት ከቀረቡት ውስጥ የዚምቧቡዌና የናይጄሪያ ስራ ፈጣሪዎችና ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ወጣቶች ይገኙበታል።
መቀመጫውን በሌጎስ ናይጄሪያ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው “ዘ ፊውቸር አፍሪካ” አፍሪካውያን ወጣቶችን በማስተሳሰር በአፍሪካ አንገብጋቢ የሆኑትን የመልካም አስተዳደርና የስራ አጥነት ችግርን ለመፍታት እንደሚንቀሳቀስ መረጃዎች ያሳያሉ።
(ኢዜአ)
20 የታሸገ ውሀ አምራቾች በግብአት እጥረት እና የዋጋ ንረት ምክንያት ሥራ አቆሙ
የኢትዮጲያ የታሸገ ውሀ እና ለስላሳ መጠጥ አምራቾች ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ መርዕድ ለኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ እንደገለጹት በታሸገ ውሀ ዘርፍ 106 ኢንዱስትሪዎች ይገኛሉ፡፡እነዚህ ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ መካከለኛ እና ዝቅተኛ አምራቾችን ያቀፉ ናቸው፡፡
የታሸገ ውሀ አምራች ዘርፍ ከፍተኛ የስራ እድል የፈጠረ ከመሆኑም ባሻገር ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ያሉበት መሆኑን አቶ አሸናፊ ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ የግብአት እጥረት እና የዋጋ መናር በኢንዱስትሪዎቹ እንቅስቃሴ ላይ አደጋ እንዲጋረጥ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡
ማህበሩ በዘርፉ ያጋጠሙትን ችግሮችን በጥናት ለይቶ ለኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ለአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በአካል እና በደብዳቤ የእንነጋገር ጥያቄ ቢያቀርብም ምላሽ አለማግኘቱን አቶ አሸናፊ ገልጸዋል፡፡ በተጠቀሱት ችግሮች ምክንያትም እስካሁን 20 የታሸገ ውሀ አምራቾች ስራ ማቆማቸውን አስታውቀዋል፡፡
ለአብነትም ፒኢፒ የተሰኘው ግብአት ከአንድ አመት ከሶሰት ወራት በፊት በኪ.ግ 53 ብር ሲሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በኪ.ግ 130 ብር ገብቷል ይህም ከእጥፍ በላይ ጭማሪ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አሸናፊ ችግሩ ከግብአቱ አምራች ኩባንያዎች ወይስ ከአስመጪዎቹ ነው የሚለውን ለመለየት እና መፍትሔ ለማስቀመጥ ቢሞከርም በሚመለከታቸው የመንግስት መ/ቤቶች በኩል ተገቢው ትብብር አልተገኘም ብለዋል፡፡
የነዳጅ ዋጋ መጨመር ለዚህ አስተዋጽኦ እንዳለው ቢታመንም አግባብ የሆነውን አካሔድ ለመወሰን እንዲያስችል ከሚመለከታቸው ጋር ውይይት ማድረጉ ወሳኝ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
አብዛኞቹ የውሀ አምራች ኢንዱስትሪዎች በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮሚያ