የመከላከያ ሠራዊቱ ሲጠቀምበት በቆየው የማዕረግ ምልክት ላይ ማሻሻያዎችን አደረገ።
የመከላከያ ሠራዊቱ ሲጠቀምበት በቆየው የማዕረግ ምልክት ላይ ማሻሻያዎችን አድርጓል። ማሻሻያው የተደረገበት ምክንያትም የሠራዊቱ ማዕረግ አገራዊም ይሁን ወታደራዊ ታሪካዊ ይዘት ያለውና የሠራዊቱንም ባህሪ ሊገልፅ የሚችል ሆኖ እንዲዘጋጅ በማስፈለጉ ነው።
በዚህም መሠረት በሠራዊታችን የማዕረግ ምልክቶች ውስጥ ጋሻና አንበሳ በዋናነት ጥቅም ላይ ውለዋል።
በአገራችን የቀደመ ታሪክም በተለይ ጋሻው በንጉሱም ይሁን በደርግ ዘመን በሠራዊቱ የማዕረግ ምልክቶች ላይ ጥቅም ላይ ውሏል። ንጉሱ ዘውድን በማዕረግ ምልክትነት ሲጠቀሙ፣ ደርግ ዘውዱን መቀየር ስለነበረበት ዘውዱን በአንበሳ ተክቶ ተጠቅሞበታል። እነዚህ ሁለቱም ታሪካዊና ወታደራዊ ምልክቶች ናቸው።
አሁን ስንጠቀምበት የቆየው የሠራዊቱ ማዕረግ እነዚህን ምልክቶች በመሰረታዊነት ነበር የቀየራቸው። በርግጥም ሲታይ ታሪካዊና አገራዊ ይዘቱ የጎላ አልነበረም። ሠራዊት ዘመን ተሻጋሪ መሆን ካለበት ዓርማውም