ኢትዮጵያዊው ዳኛ ባምላክ ተሰማ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚደረገውን ወሳኝ ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመራል
ኢትዮጵያዊው ዳኛ ባምላክ ተሰማ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚደረገውን ወሳኝ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በዋና ዳኝነት እንደሚመራ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስታወቀ።
33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለግማሽ ፍጻሜ ያለፉ አራት አገራት ነገ እና ከነገ በስቲያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን፤ በነገው እለት ምሽት አራት ሰዓት ቡርኪናፋሶ ከሴኔጋል ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ካፍ እንዳስታወቀው፤ ለፍጻሜ ለማለፍ የሚደረገውን ይህን ጨዋታ ኢትዮጵያዊው ዳኛ ባምላክ ተሰማ በዋና ዳኝነት ይመራዋል፡፡
በተጨማሪ ሱዳናዊው ሙሀመድ አብዱላሂና ኬኒያዊው ጊልበርት ችሮይት ደግሞ በረዳትነት ዳኝነት ጨዋታውን የሚመሩት ይሆናል፡፡
ከነገ በስቲያ ምሽት አራት ሰዓት ደግሞ የውድድሩ አስተናጋጅ ካሜሩን እና ግብጽ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ይታወቃል፡፡(ENA)