የአርቲስት ኒና ግርማ ማጀቴ የሙዚቃ አልበም ነገ ይለቀቃል
"ማጀቴ" የተሰኘው አዲስ የሙዚቃ አልበም በመጪው ሐሙስ ለአድማጭ ይደርሳል።
በሻኩራ ሪከርድስ የተዘጋጀው "ማጀቴ" የተሰኘው አልበም ሀሙስ የካቲት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ለአድማጭ እንደሚደርስ አዘጋጆቹ ትላንት በቀነኒሳ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርገዋል።
ይህ አልበም የራፕ ዘፈኖችን በማቀንቀን የምትታወቀው ኒና ግርማ የመጀመሪያ አልበም ሲሆን፥ በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ስራዎችንም አካቷል።
በካሙዙ ካሳ የተቀናበረው የማጀቴ አልበም የግጥም እና ዜማ ድርሰት በኒና ግርማ የተሰራ እንደሆነና በሻኩራ ሪከርድስ አማካይነት ፕሮዲዩስ እንደተደረገም ተገልጿል።