አራት የሬዲዮ ብሮድካስት ባለፈቃዶች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለአራት ሬዲዮ ብሮድካስት ባለፈቃዶች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ፡፡
ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው ሬዲዮ ብሮድካስት ባለፈቃዶችም ፣ ሟርሴ መልቲሚዲያ ኃ.የተ.የግ.ማ.(ጄ ሬዲዮ ጣቢያ 106.7 ) ፣ አዲስ ኦንላይን የግንኙነትና የግብይት ሥራ ኃ.የተ.የግ.ማ.(ሀበሻ ኤፍ.ኤም. ሬዲዮ 98.7) ፣ትርታ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ. (ትርታ ሬዲዮ 97.6) እና ኢትዮ ዋርካ መልቲ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን አ.ማ (ዋርካ ሬዲዮ 104.1) መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ባለስልጣኑ ጉዳዩን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው ማብራሪያ፥ ጄ ሬዲዮ ጣቢያ 106 ነጥብ 7 የተሰኘው ባለፈቃድ የሬድዮ ፈቃዱን ካገኘ ጀምሮ ሙዚቃ ብቻ በማጫወት በውድድር ፈቃድ ከወሰደበት ውል ውጪ እየሰራና ውስን የሆነውን የሬድዮ ሞገድ ከታለመለት አላማ ውጪ ለብክነት እየዳረገ ይገኛል ብሏል፡፡
በውድድር የሚገኝን ይህን ውድ የሀገርና የህዝብ ሀብት ለተፈቀደው እና ውል ለተገባበት አላማ እንዲውል በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በተደጋጋሚ ጊዜ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ቢሆንም በድርጅቱ በኩል የተለወጠ ነገር አለመኖሩ ተጠቁሟል፡፡
ስለዚህም ሬድዮ ጣቢያው እስከ መጋቢት 01 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ውል በገባው መሰረት መደበኛ ስርጭቱን ካልጀመረ ፈቃዱ በቀጥታ እንደሚሰረዝ ባለስልጣኑ አስጠንቅቋል፡፡
በሌላ በኩል አዲስ ኦንላይን፣ ትርታ ትሬዲንግ እና ኢትዮ ዋርካ የተሰኙ ድርጅቶች በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 80 መሠረት ከባለሥልጣን መ/ቤቱ የንግድ ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ ወስደው ከአንድ ዓመት በላይ ቢሞላቸውም በህጉ መሰረት መደበኛ ስርጭት ባለመጀ